AMN- መስከረም 9/2017 ዓ.ም
በምስራቅ ወለጋ ዞን በጅማ አርጆ ወረዳ በሁንዴ ጉዲና ቀበሌ ለአሸባሪው ኦነግ ሸኔ መረጃ ሲያቀብሉና የሎጀስቲክ ድጋፍ ሰጪ በመሆን ለጥፋት ተልዕኮ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ የሽብር ቡድኑ ተላላኪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል አስጨንቅ ፅጌ አስታወቁ።
ሠራዊቱ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና የአሸባሪዎችን እንቅስቃሴ የመከታተልና የመቆጣጠር ስራ ከአካባቢው የፀጥታ ሃይሎች ጋር ቅንጅት በመፍጠር እያከናወነ መሆኑን ከፍተኛ መኮንኑ አረጋግጠዋል።
በየትኛውም ጊዜ የሽብር ቡድኑን መረጃ በማቀበልና የሎጅስቲክስ ድጋፍ በመስጠት በተለያዩ መንገዶች የሚደግፉትን በቁጥጥር ስር የማዋል እና ግንኙነታቸውን የመበጣጠስ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አዛዡ ገልፀዋል ።
ከህብረተሰቡ ሊሰወርና ሊደበቅ የሚችል ምንም ነገር ባለመኖሩ የሽብር ቡድኖችን አላማ በመቃወምና አጋልጦ በመስጠት ለሰላም ከህብረተሠቡ ጋር በጋራ እየተሠራ መሆኑን ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ የትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።