መሳይ ተፈሪ  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት እንደሚመራ ፌደሬሽኑ አስታወቀ

You are currently viewing መሳይ ተፈሪ  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት እንደሚመራ ፌደሬሽኑ አስታወቀ
  • Post category:ስፖርት

AMN- ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣርያ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎችን በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነትይመራል ሲል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ላለፉት 12 ወራት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ ሆነው ሲሰሩ እንደቆዩ የሚታወቅ ሲሆን ቡድናችን ከኤርትራ ጋር የሚያከናውናቸውን ጨዋታዎች ጨምሮ የቻን ማጣርያን በጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝነት እንደሚመሩት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review