AMN- መስከረም 9/2017 ዓ.ም
ሦስት ሕገ-ወጥ የከረሜላ ምርቶች ገበያ ላይ እንዳይውሉ መታገዳቸውን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
ሃኒ ስዊት፣ ላቭሊ ካንዲ እና ጎግል ካንዲ የተሰኙ የከረሜላ ምርቶች ናቸው ገበያ ላይ እንዳይውሉና ሕብረተሰቡም እንዳይጠቀማቸው የታገዱት፡፡
ምርቶቹ ብሔራዊ አስገዳጅ ገላጭ ጽሑፍ ደረጃ CES 73/2013 ሳያሟሉ ገበያ ላይ የተገኙ ሲሆን÷ ማን እንዳመረታቸው፣ የት ሀገር እንደተመረቱና የአምራቹ አድራሻ እንደማይታወቅ ተጠቅሷል፡፡
ሕብረተሰቡ መሰል ጤናን የሚጎዱ ምርቶች ሲያጋጥመው በነጻ የስልክ መስመር 8482 ወይም በአቅራቢያ ላሉ የጤና ግብዓት ተቆጣጣሪ ተቋማት አሊያም ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ባለስልጣኑ በመረጃው ጥሪ አቅርቧል፡፡