AMN- መስከረም 20/2017 ዓ.ም
በመዲናዋ ያለንግድ ፈቃድ፣ ባልታደሰ ንግድ ፈቃድና በተሰረዘ ንግድ ፈቃድ ሲነግዱ የተገኙ 1ሺህ 441 የንግድ ድርጅቶች መታሸጋቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ “ በሁሉም የንግድ መንደሮች የነግድ ህጋዊነትን እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ሀሳብ ከነሀሴ 27/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባካሄደው የንግድ ቁጥጥር ያለንግድ ፈቃድ፣ ባልታደሰ ንግድ ፈቃድና በተሰረዘ ንግድ ፈቃድ ሲነግዱ ያገኛቸውን የንግድ ድርጅቶች ማሸጉን አመልክቷል፡፡
በዛሬው እለት በቢሮው የንግድ ሪጉላቶሪና ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ አሰፋ እንዳመለከቱት ከነሀሴ 27 /2016ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 18/2017ዓ.ም ድረስ በ69 ሺህ 50 የንግድ ድርጅቶች ላይ ክትትል ተደርጓል፡፡
በዚህም 1 ሺህ 400 የንግድ ድርጅቶች ያለ ንግድ ፈቃድ፣ 71 ባልታደሰ ንግድ ፈቃደችና 2 በተሰረዘ ንግድ ፈቃድ ሲነግዱ መገኘታቸው በመግለፅ 1 ሺህ 441 የንግድ ድርጅቶች መታሸጋቸውና ለ32ቱ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ተገልፆል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በተደረገው ክትትልና ቁጥጥር 703 የንግድ ድርጅቶች ልዩ ልዩ ጥፋቶችን ፈፅመው በመገኘታቸው እንዲያርሙ መደረጉን መግለጻቸውን ከቢሮው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡