በመዲናዋ ከአማረኛ ቋንቋ በተጨማሪ በሶስት ቋንቋዎች የመንጃ ፍቃድ ስልጠና ለመሰጠት ዝግጅት ተጠናቋል

You are currently viewing በመዲናዋ ከአማረኛ ቋንቋ በተጨማሪ በሶስት ቋንቋዎች የመንጃ ፍቃድ ስልጠና ለመሰጠት ዝግጅት ተጠናቋል

AMN-ሚያዝያ 25/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ከአማረኛ ቋንቋ በተጨማሪ በሶስት ቋንቋዎች የመንጃ ፍቃድ ስልጠና ለመሰጠት ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ከአማረኛ ቋንቋ በተጨማሪ በሌሎች ቋንቋዎችም የንድፍ ሃሳብ ስልጠና እንዲሰጥ ጥያቄ ሲቀርብ እንደነበረ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ በድሉ ሌሊሳ ተናግረዋል፡፡

ይህ በመሆኑም የንድፍ ሃሳብ የፈተና ውጤት ምጣኔም ከ56 ከመቶ ያልበለጠ እንደነበረም ምክትል ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

ይህንን የረዥም ጊዜ የመልም አስዳደር ጥያቄ ለመመለስ አሁን ላይ ከአማረኛ ቋንቋ በተጨማሪ በሶስት የሀገር ውሥጥ ቋንቋዎች የመንጃ ፍቃድ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁንም ምክትል ስራ አስኪያጅ አስታውቀዋል፡፡

በሶስቱ ተጨማሪ ቋንቋዎች ለማሰልጠን ፍቃደኛ ለሆኑ 12 ማሰልጠኛ ተቋማት ፍቃድ መሰጠቱንም የአዲስ አበባ ከተማ የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ በድሉ ሌሊሳ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ከ137 በላይ የመንጃ ፍቃድ ማስለጠኛ ተቋማት እንዳሉም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review