በመዲናዋ ውስብስብ የሆኑ ወንጀሎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታወቀ Post published:May 7, 2025 Post category:መልካም አስተዳደር AMN – ሚያዝያ 29/2017 በመዲናዋ ሲያጋጥሙ የነበሩ ውስብስብ የሆኑ ወንጀሎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል፡፡ በመዲናዋ በመቀናጀት በተሰሩ ስራዎች በአደባባይ የተከበሩ በዓላት እና ኮንፈረንሶች ያለምንም ችግር መከናወናቸውን የአዲስ አበባ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ተናግረዋል። ለስራ ምቹ የሆነ፣ ተወዳዳሪና ደረጃውን የሚመጥን ተቋም የመገንባት ስራ ሰላምን ከማስፈን ጎን ለጎን ስለመከናወኑም ኮሚሽነር ጌቱ አመላክተዋል፡፡ የማህበረሰቡን ሰብዓዊ መብቶች የጠበቀ ህጋዊና አስተዳደራዊ አገልግሎት የመስጠት ስራ በአዲስ አበባ ፓሊስ የተከናወነ እና እየተከናወነ ያለ ተግባር መሆኑም ተመላክቷል፡፡ ከአፍሪካ አምስት ከተሞች የአዲስ አበባ ፓሊስን በአገልግሎት አሰጣጡ ተጠቃሽ ለማድረግ በቴክኖሎጅ የታገዘ ተቋም መገንባት ላይ በትኩረት ስለመሰራቱ ተጠቅሷል። አዲስ አበባን ከወንጀልና ከፀጥታ ስጋት የፀዳች ከተማ ለማድረግ ተቋሙ፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባከናወናቸው ተግባራት ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ይገኛሉ። በንጉሱ በቃሉ 0 Reviews ( 0 out of 0 ) Write a Review Submit Review You Might Also Like ከ31 ሺህ በላይ የሁለተኛ ምዕራፍ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ሽግግር በነገው ዕለት ይካሄዳል፡- ሥራና ክህሎት ቢሮ January 4, 2025 በሀገር ጉዳይ እኩል የመወሰንና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጉዳይ በለውጡ መንግስት ምላሽ አግኝቷል April 11, 2025 በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ፍጥነት፣ ጥራት እና የሀብት አጠቃቀም የሚደነቅ ነው- አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር February 18, 2025
በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ፍጥነት፣ ጥራት እና የሀብት አጠቃቀም የሚደነቅ ነው- አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር February 18, 2025