
AMN – ግንቦት 1/2017 ዓ.ም
በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 121 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ትኩረት በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 41 ኢትዮጵያውያን ከትናንት በስቲያ ረዕቡ ዕለት የተመለሱ መሆኑ የተገለጸ ሲሆኑ 80ዎቹ ደግሞ ዛሬ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሕንድ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል በማይናማር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡
መንግሥት ሕብረተሰቡ በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሀሰተኛ ቅስቀሳ ተታሎ የሥራ ስምሪት ውል ወደ አልተፈጸመባቸው አገራት ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንዲቆጠብ አሳስቧል።