በሲዳማ ክልል የቱሪዝም፣ ንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑ ተገለፀ

AMN ህዳር 19/2017 ዓ.ም

በሲዳማ ክልል የቱሪዝም፣ ንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶች አበረታች መሆናቸው ተገልጿል።

የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሲዳማ ክልል ሀዋሳና አጎራባች ከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ የንግድ ቱሪዝምና ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች በመመልከት ላይ ይገኛል።

በክልሉ በቱሪዝም ፣ በንግድ ኢንቨስትመንትና ሆቴል ዘርፍ ላይ በተሰማሩ የግልና የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቋሚ ኮሚቴው ምልከታ አድርጓል።

ክልሉ ያለውን ዕምቅ የቱሪዝም አቅም በማሳደግ የጎብኝዎችን ቁጥር ለመጨመርና መዳረሻ ስፍራዎችን ምቹ ለማድረግ የተደረጉ ጥረቶች በኮሚቴው ተዳሰዋል።

በሲዳማ ክልል በቅዳሜ ገበያ ለከተማው ማህበረሰቡ የሚቀርቡ ምርቶች የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችና የመንግስት ሰራተኞች በህብረት ሥራ ማህበራት አማካኝነት የግብርናና ሌሎች ግብዓቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ የሚደረገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑ ተገልጿል።

ከክልሉ ሸማች ማህበራትና ከንግድ ዘርፍ ማህበራት ጋር ቋሚ ኮሚቴው ተወያይቷል።

በግል ኢንቨስተሮች በመልማት ላይ የሚገኙ የዶሮ ዕርባታና መኖ ማቀነባበሪያ፣ የተጣራ ውሃ ፋብሪካ እንዲሁም የይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪያል ፖርክ ምልከታ እንደተደረገባቸው ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review