“ጠንካራ የሲቪል ማህበራት ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪ ሃሳብ በየካ ክፍለ ከተማ ውይይት ተካሂዷል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በሀገረ መንግስት ግንባታ ውስጥ በተለይም ጠንካራ ተቋማት እንዲፈጠሩ ፣ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲገነባ ፣ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሀኑ ረታ ተናግረዋል፡፡
ዘርፉ በአግባቡ ከተመራ የሲቪክ ባህሉ የዳበረ ማህበረሰብ እንዲገነባ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያበረክት እንደሚችልም ገልጸዋል።
መንግስት ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሁለንተናዊ መልኩ የበለፀገች ሀገር ለመገንባት ከፍተኛ ትኩረት ከሰጣቸው መስኮች አንዱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች መሆናቸውንም ዋና ስራ አስፈፃሚው አንስተዋል።
በአሸናፊ በላይ