በኢራቅ አሸዋ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ በርካቶችን ለመተንፈሻ ችግር መዳረጉ ተሰማ

You are currently viewing በኢራቅ አሸዋ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ በርካቶችን ለመተንፈሻ ችግር መዳረጉ ተሰማ

AMN – ሚያዝያ 07/2017

በማዕከላዊ እና ደቡባዊ የሀገሪቱ ክፍሎች የተከሰተው አሸዋ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ አንድ ሺ 800 ዜጎችን ለመተንፈሻ አካል ችግር መዳረጉ ተገልጿል፡፡

አውሎ ንፋሱ የሀይል አቅርቦትን እና የአየር በረራዎችንም አስተጓጉሏል፡፡ ለመተንፈሻ ችግር ከተጋለጡ ሰዎች መካከል በርካቶች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ ናቸው ብሎ ካስቀመጣቸው 5 የዓለም ሀገራት መካከል ኢራቅ አንዷ ናት፡፡ በተደጋጋሚም አሸዋ በቀላቀለ አውሎ ንፋስ፣ በከፍተኛ ሙቀት እና በውሃ እጥረት የምትቸገር ሀገር መሆኗን ቢቢሲ ነው የዘገበው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review