AMN – ታኅሣሥ 13/2017 ዓ.ም
ሰባተኛ ቀኑን በያዘው የኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር ምዕራፍ በኦሮሚያ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እና በቅርቡ ከመንግስት ጋር ስምምነት የፈፀሙ ግለሰቦችን ጨምሮ የፖለቲካ ፓርቲዎች ፣ የመንግስት ተወካዮች እና የማህበረሰብ መሪዎች የአጀንዳ ማሰባሰብ ምክክር ተጀምሯል።
የሃይማኖት ተቋማት ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና ማህበራትም በመጪው ሀገር አቀፍ የምክክር ጉባኤ ላይ መግባባት ሊደረስባቸው ይገባል ባሏቸው ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው።
ተሳታፊዎች ሀገራዊ መግባባት ሊደረሰባቸው ይገባል የሚሏቸውን መሰረታዊ ጉዳዮች በማንሳት የተስማሙባቸውን የጋራ አጀንዳዎች ለኮሚሽኑ የሚያቀርቡ ይሆናል።
በካሳሁን አንዱዓለም