በኮሪደር ልማት የተገነቡ ተርሚናሎች የትራንስፖርት አገልግሎቱን እያሳለጡ ነው፡-አሽከርካሪዎች

You are currently viewing በኮሪደር ልማት የተገነቡ ተርሚናሎች የትራንስፖርት አገልግሎቱን እያሳለጡ ነው፡-አሽከርካሪዎች

AMN -ጥቅምት 1/2017 ዓ.ም

በኮሪደር ልማት የተገነቡ ተርሚናሎች የትራንስፖርት አገልግሎቱን እያሳለጡ መሆኑን አሽከርካሪዎች ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ከአካተታቸው ልማቶች መካከል የታክሲና አውቶብስ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናል ግንባታ ይገኝበታል፡፡

በሁሉም የኮሪደር ልማት አቅጣጫዎች በርከት ያሉ የተርሚናል ግንባታዎች እየተከናወኑ ሲሆን ከፊሎች አገልግሎት በመስጠት ላይም ይገኛሉ፡፡

በሜክሲኮ አካባቢ የተገነባው የአውቶቢስና ታክሲ ተርሚናልም ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

ለኤ ኤም ኤን አስተያየታቸውን የሰጡ አሽከርካሪዎችና የስምሪት ባለሙያዎችም በአካባቢው ከዚህ ቀደም ደረጃውን የጠበቀ የታክሲ መጫኛና ማውረጃ ተርሚናል ባለመኖሩ ሲቸገሩ መቆየታቸውን አንስተው አሁን ላይ ስርዓት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል፡፡

አገልግሎት እየሰጠ ባለው ተርሚናል የአውቶቢስና የታክሲ መጫኛና ማውረጃ ተለይቶ ህብረተሰቡም አገልግሎቱን በአግባቡ እንዲያገኙ እያስቻለ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በፊርደውስ አብዱልሐኪም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review