በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ “የኢሬቻ ኤክስፖ 2017” ሊካሄድ ነው

You are currently viewing በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ “የኢሬቻ ኤክስፖ 2017” ሊካሄድ ነው

AMN-መስከረም 8/2017 ዓ.ም

የኦሮሚያ ባህል እና ቱሪዝም ከሀገሬ ኢቨንትስ እና ፕሮሞሽን ጋር በመተባበር በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን “የኢሬቻ ኤክስፖ 2017” እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ኤክስፖው የኦሮሞ ህዝብ እና ወንድም ኢትዮጵያውያን ባህላዊ ትውፊትን የሚያከብር ብቻ ሳይሆን የተለያዩ የንግድ ኤግዚቢሽን የሚቀርቡበት መሆኑ ተገልጿል።

በተጨማሪም ባህላዊ መገለጫዎች ላይ ያተኮሩ ትዕይንቶችም የኤክስፖው አካል መሆናቸውም ተጠቅሷል።

በኤክስፖው ከ200 ሺ በላይ ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተመላክቷል።

ኤክስፖው ከመስከረም 18 -24 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በሐብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review