በ17ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ኢትዮጵያ ቡና ሁለተኛው የፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል

You are currently viewing በ17ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ኢትዮጵያ ቡና ሁለተኛው የፍፃሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል

ተጠባቂ በነበረው የሸገር ደርቢ የኢትዮጵያ ቡና እና የቅዱስ ጊዮርጊስ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ መደበኛው ደቂቃ አንድ አቻ ሲጠናቀቅ ለቅድሱ ጊዮርጊስ አሮን ሀንተር እንዲሁም ለኢትዮጵያ ቡና ወልደአማኑኤል ጌቱ ግቦቹን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።

ለዋንጫ የሚያልፈውን ቡድን ለመለየት በተሠጠው የመለያ ምት ኢትዮጵያ ቡና 5ለ4 በማሸነፍ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ለፍፃሜ እንደሚጫወት አረጋግጧል።

በጨዋታው ላይ የኢትዮጵያ ቡናው የመስመር ተከላካይ በፍቃዱ አለማየሁ የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።

የ17ኛ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የደረጃ እና የፍፃሜ ጨዋታዎች የፊታችን ሐሙስ የሚደረጉ ሲሆን ለደረጃ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ኢትዮጵያ መድህን ለፍፃሜ ደግሞ ኢትዮጵያ ቡና ከሀዲያ ሆሳዕና በ7:00 እና በ9:00 ይጫወታሉ።

በአብርሃም አድማሱ

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr

Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9

Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8

Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review