AMN – ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በ2017 የትምህርት ዘመን ከ23 ሺህ 800 በላይ አዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር አበራ ብሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በመዲናዋ የተሟላ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስጠት የሚችሉ 14 ኮሌጆች ሰልጣኞችን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል ።
በዘንድሮው የትምህርት ዘመንም 23 ሺህ 800 ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ዝግጅት መደረጉንም ተናግረዋል ::
ምዝገባዉ ከጥቅምት 15 ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በኦንላይን ይከናወናልም ብለዋል ምክትል ቢሮ ሀላፊው ::
ቢሮዉ በ2017 በጀት ዓመት ከሚሰጠው መደበኛ ስልጠና በተጨማሪ ከ300 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች አጫጭር ስልጠና እንደሚሰጥም ተናግረዋል ::
በቴዎድሮስ ይሳ