AMN- መስከረም 28/2017 ዓ.ም
በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ቀርሳ አቦ ከኔ ቀበሌ ላይ የምዕራብ ዕዝ ኮር ባደረገው ስምሪት የሽብር ቡድኑ ከነ ሙሉ ትጥቁ ለመከላከያ ሰራዊት እጅ እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የኮሩ አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ሀብታሙ ምህረቴ አሁን ላይ የኮሩ ሰራዊት በሽብር ቡድኑ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ አካባቢውን ከስጋት ነፃ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀው የሰራዊታችንን ምት መቋቋም የተሳነው ይህ የሽብር ቡድን በየጊዜው እርስ በእርሱ እየተታኮሰ ከመሆኑም በተጨማሪ በተገኘው ክፍተት ሁሉ ለሠራዊታችን እጅ እየሰጠ ይገኛልም ብለዋል።
እያደረግን ያለውን ስምሪት አጠናክረን እንቀጥላለን ያሉት ጀኔራል መኮንኑ ጃን ቃንቂ ከሚባል የሽብር ቡድኑ መሪ አባላት መካከል ሶስት ክላሽና አስራ ሁለት የክላሽ ካዝና ሶስት የወገብ ትጥቅን ጨምሮ ከሰማንያ በላይ የክላሽ ጥይት ጋር ለኮሩ ሰራዊት እጅ መስጠታቸውን አዛዡ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።