አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጅማ ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

You are currently viewing አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጅማ ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

AMN – ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በጅማ ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የሚመራው የሥራ ሀላፊዎች ቡድን ሰሞኑን በኢሉአባቦር እና በቡኖ በደሌ ዞኖች የተለያዩ የልማት ስራዎችን ተመልክቷል።

በዞኖቹ በነበራቸው የልማት ስራዎች ጉብኝት የክልሉ መንግስት የተገበራቸው የግብርና ልማት ኢንሼቲቮች ተስፋ ሰጪ መሆናቸው ተገልጿል።

ከግብርና ልማት ኢንሼቲቮች መካከል የሻይ ቅጠል፣ የሩዝ፣ የቡና፣ የማር እና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በተሻለ መልኩ እየተከናወነ መሆኑ ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review