AMN-ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ጅምናስቲክ ፌደሬሽ ፕሬዘዳንት የሆኑት አቶ ገበየሁ ታከለ የኢንተርናሽል ጅምናስቲክ ፌደሬሽን አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡
85ኛው የኤፍ አይ ጂ ኮንግረስ በኳታር ዶሃ ሲካሄድ በቀጣይ ኢንተርናሽል ፌደሬሽኑን የሚመሩ አካላት መመረጣቸውን ፌደሬሽኑ በድህረ ገፁ ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡
ከተመረጡት 4 አፍሪካውያን መሪዎች መካከል አቶ ገበየሁ በኢትዮጵያ ጅምናስቲክ ስፖርት ላይ ከሁለት አስርት አመታታት በላይ አገልግለዋል፡፡
ጃፓናዊው ሞሪናሪ ዋታናቤ በድጋሚ ለ3ኛ ጊዜ የኢንተርናሽል ፌደሬሽኑን በፕሬዝዳንትነት የተመረጡበት መድረክ አቶ ገበየሁ የካውንስል አባል መሆናቸው ስፖርቱን ለማነቃቃት ትልቅ አጋጣሚ እንደሚፈጥር ይጠበቃል፡፡
164 የዓለም ሀገራት የኢንተርናሽሉ ጅማስቲክ ፌደሬሽን አባል ሲሆኑ፤ በዘንድሮው መድረክ ኬኒያ ፤ ኮትዲቫር፤ ጊኒና ዛምቢያ ከአፍሪካ የአባልነት ጥያቄአቸው ተቀባይነት አግኝቷል፡፡
86ኛው የኤፍ አይ ጂ ኮንግረስ በባንኮክ ታይላንድ እንደሚካሄድም ተመላክቷል፡፡