AMN – ታኀሣሥ 28/2017 ዓ.ም
አዋሽ ኢንሹራንስ አ.ማ. የዲሬክተሮች ቦርድ፣ የማኔጅመንት አባላት እና መላው ሰራተኞች በአቶ ቡልቻ ደመቅሳ ህልፈተ የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
ባንኩ ባወጣው የሀዘን መግለጫ ፣ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ በህይወት በነበሩበት ዘመን የትላልቅ ስኬቶች ባለቤትና ትልቅ የሀገር ባለ ዉለታ እንደነበሩ ገልጿል።
አቶ ቡልቻ የሀገራቸው እና የአለም ምጣኔ ሃብት ዉስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እንደነበሩም በመግለጫው ተመላክቷል።
አቶ ቡልቻ በዛ ዘመን ከሌሎች የስራ ባልደረቦቻቸዉ እና የሙያ አጋሮቻቸዉ ጋር በመሆን ዘመን ተሻጋሪ ራዕይ በመሰነቅ፣ የዛሬዉን ስኬታማ አዋሾች (አዋሽ ኢንሹራንስ እና ባንክ) ከመሰረቱት አንዱ ነበሩ ሲል ባንኩ ገልጿል፡፡
አዋሽ ባንክን በተለያዩ ከፍተኛ ሀላፊነት የመሩ፣ የሀገራችን የወቅቱ የፋይናንስ ምክትል ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ፣ ሀገራቸውን ወክለው በዓለም ባንክ ቦርድ ያገለገሉ እና የሀገራቸዉን ህዝብ መብት ለማስከበር የታገሉና የፓርላማ አባል ሆነው ያገለገሉ ትልቅ የሀገር ባለዉለታ እንደነበሩም ተገልጿል።
ባንኩ በአቶ ቡልቻ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን በመግለጽ ፈጣሪ ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት እንዲያኖር ተመኝተዋል፡፡
All reactions:
219Abate Feyissa and 218 others