የተጠናቀቀው በጀት ዓመት አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሁለንተናዊ ለውጦችን ያስመዘገበበት ዓመት ነበር፡- ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ካሳሁን ጎንፋ

You are currently viewing የተጠናቀቀው በጀት ዓመት አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሁለንተናዊ ለውጦችን ያስመዘገበበት ዓመት ነበር፡- ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ካሳሁን ጎንፋ

AMN – ሀምሌ 6/2016 ዓ.ም

የ 2016 በጀት ዓመት አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ሁለንተናዊ ለውጦችን ያስመዘገበበት ታላቅ ዓመት ሆኖ ማለፉን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለጹ ።

ለተመዘገበዉ ሁለንተናዊ ውጤትም የተቋሙ አመራር እና ፈጻሚ ሚና ተኪ የለውም ሲሉ እዉቅና ሰጥተዋል ።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም እና የ 2017 በጀት ዓመትን እቅድ ገምግሟል።

ሚዲያው በ2016 በጀት ዓመት በይዘት ስራዎቹ የህዝብ ድምጽ መሆኑን በተጨባጭ ማሳየቱ ተገልጿል ።

የይዘት ስራዎቹ ተአማኒነትን ያገኙበትና በተግባር የታዩበት ዓመትም ነበር ተብሏል።

ኤኤምኤን በበጀት ዓመቱ ያስገኘዉ ከፍተኛ ገቢም ተወዳዳሪነቱንና ያተረፈዉን እዉቅና እንደሚያመላክትም ተገልጿል።

ጠንካራ አመራር ፣አዳዲስ ፎርማቶችን መቅረጽ ፣አዲስ የቋንቋዎች ቻናል መክፈቱ ፣ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ግንባታን ማስጀመሩ ፣የይዘት ስራዎቹ መሸጣቸዉ ፣የሌሎች ተቋማት ልምድ መቅሰሚያ መሆን መቻሉ በበጀት አመቱ በጥንካሬ ከተነሱት ተግባራት ጥቂቶቹ ናቸዉ።

የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ባስተላለፉት መልእክት ተቋሙ ባመጣዉ ትልቅ ለዉጥ የህዝብ ችግር ፈቺ መሆኑን በተግባር አሳይቷል ብለዋል።

በበጀት አመቱ በተገኙ ታላላቅ ድሎች ሳንኩራራ ተወዳዳሪና ቀዳሚ የሚያደርጉን ስራዎች ላይ ልዩ ትኩረት እናደርጋለንም ብለዋል።

የብዝሃነትን ሚና ማጠናከር ፣መዝናኛዉ ላይም ልዩ ትኩረት መስጠት የህዝብ ድምጽ ሆኖ ማገልገልን ይበልጥ ማጠናከር አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ በቀጣይ ካስቀመጣቸዉ ግቦች ጥቂቶቹ መሆናቸውም ተመልክቷል ።

በአለማየሁ አዲሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review