አዲስ አበባ በፍይናንስ ስርዓት ፈጣን ለውጥ ከታዩባቸው የአፍሪካ ከተሞች ግንባር ቀደሙን ድርሻ ያዘች

You are currently viewing አዲስ አበባ በፍይናንስ ስርዓት ፈጣን ለውጥ ከታዩባቸው የአፍሪካ ከተሞች ግንባር ቀደሙን ድርሻ ያዘች

AMN – ታኀሣሥ 10/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ ባደረጉት ጥናት በፍይናንሻል አስተዳደር ስርዓት አተገባበር የተሻሉ እንቅስቃሴዎች እና ፈጣን ለውጥ ከታዩባቸው የአፍሪካ ከተሞች መካከከል አዲስ አበባ አንዷ መሆኗ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ ከኮቪድ-19 ጀምሮ የነበረውን የገቢ አሰባሰብ እና የፋይናስ ስርዓት መሰረት ያደረገ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ ሪፖርቱን የተመለከተ ግምገማም በቢሾፍቱ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር)ን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የስራ ኃላፊዎች እና ባለ ድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

በሪፖርቱም ጥናቶች ከተከናወኑባቸው የአፍሪካ ከተሞች መካከል አዲስ አበባ ሀብትን በማመንጨት፣ ያመነጨችውንም ሀብት ወደስራ በመቀየር ረገድ እና በተለያዩ መስፈርቶች የተሻለ ውጤት ማስመዝገቧ ተገልጿል።

የጥናቱ ዓላማ ጤናማነትንና ዘለቄታዊነትን የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎችን ለማውጣትና ቀጣይ እርምጃዎችን ለመውሰድ በር የሚከፍት ስለመሆኑ ተመላክቷል፡፡

በተለይ አዲስ አበባ ሀብት ከማሰባሰብም ባሻገር ሀብት ለማመንጨት የምትሄድባቸው እርቀቶች ግንባር ቀደም እንደሚያደርጋት ተነስቷል።

አዲስ አበባ በአፍሪካ እራሳቸውን በራሳቸው ከሚያስተዳድሩና ገቢ ከሚያመነጩ የአህጉሪቱ ከተሞች አንዷ መሆኗ የተጠቆመ ሲሆን፣ ለዚህም እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ማረጋገጫ ስለመሆናቸውም በመድረኩ ተመላክቷል።

በራሔል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review