አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ዛሬ ይመረቃል

You are currently viewing አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ዛሬ ይመረቃል

AMN – የካቲት 22/2017 ዓ.ም

ማዕከሉ ደረጃውን የጠበቀ አህጉር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሁነቶችን ለማስተናገድ በሚያስችል ሁኔታ ነው የተገነባው፡፡ ይህ ማዕከል በ40 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድ ጊዜ ከ10 ሺህ በላይ ሰዎችን ማስትናገድ ይችላል።

ማዕከሉ፣ ከ 3ሺህ እስክ 4ሺህ ሰዎችን የሚያስትናግዱ ሁለት ትልልቅ አዳራሾች እና ከ100 ሰው በላይ መያዝ የሚችሉ ስምንት አነስተኛ አዳራሾችን በውስጡ የያዘ ነው፡፡

በተጨማሪም እስከ 1 ሺሕ ሰዎችን የሚያስተናግዱ የእንግዳ ማረፊያዎችን የያዙ 2 ሆቴሎች ያሉት ሲሆን፣ ሬስቶራንቶች፣ የንግድ ሱቆች፣ ባንኮች እንዲሁም ሌሎችም አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በውስጡ ያካተተ ነው፡፡

ማዕከሉ ከቤት ውጪ እስከ 50 ሺሕ ሰዎችን ማስተናገድ የሚችል የኤግዚቢሽን ስፍራ እና ሁለት አንፊ ቴአትሮች ያሉት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ትልቁ የኮንፍራንስ ማዕከል ነው።

ከመስቀል አደባባይ ቀጥሎ ሁለተኛው ግዙፍ አደባባይ ከሆነው የለሚ ፓርክ ጋር ተያይዞ የተሰራው ይህ ማዕከል፣ አለም አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ሁነቶችን በብቃት የማስተናገድ አቅም ያለው ሲሆን እስከ 2 ሺሕ መኪናዎችን ማስተናግድ የሚችል የማቆምያ ስፍራ አለው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review