አዲስ የተመረጡ የምክር ቤት አባላት ቃለ-መሀላ ፈጸሙ

You are currently viewing አዲስ የተመረጡ የምክር ቤት አባላት ቃለ-መሀላ ፈጸሙ

AMN- መስከረም 27/2017 ዓ.ም

የ6ኛው ዙር ቀሪና እና ድጋሚ ምርጫ ያሸንፉ አዲስ የምክር ቤት አባላት በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ ተገኝተው ቃለ-መሀላ ፈጽመዋል፡፡

አባላቱ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም.፤ በተካሄደው ምርጫ የተመረጡ ሲሆን የምክር ቤቱ አፈ-ጉባዔ የተከበሩ ታገሰ ጫፎና የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በተገኙበት ነው ቃለ-መሀላ የፈጸሙት፡፡

በዕለቱ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት ቃለ-መሃላውን ያስፈጸሙ ሲሆን አዲስ የተመረጡ የምክር ቤት አባላትም ስራቸውን በሚጀምሩበት ወቅት በሕገ-መንግስቱ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት እንዲሁም ህግና ሥርዓትን መሰረት በማድረግ ስራቸውን ለመወጣት ቃል መግባታቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review