AMN- ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም
አፍሪካውያን ለአሁጉራቸው ሰላም እና አንድነት በጋራ መቆም ከቻሉ የማይሻገሩት ችግር አለመኖሩን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ አስገነዘቡ ፡፡
አፍሪካ በጠንካራ አንድነት ፣ለሁለንተናዊ ፀጥታና ሰላም!” በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የመጡ የመከላከያ ሚንስትሮች እና ወታደራዊ አታሼዎች በተገኙበት በአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም እየተካሄደ ነው።
በአፍሪካ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሽብርተኝነት ተግብር እየሰፋ መጥቷል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ተመስገን አፍሪካውያን ለአሁጉራቸው ሰላም እና አንድነት በጋራ መቆም ከቻሉ ሽብርተኝነትን እና መሰል ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት ይችላሉ ብለዋል።
በሃገራት የሚፈጠሩ የሽብር ቡድኖች እና ሽብርተኛነትን በተናጠል ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶች ሃገራትን ዋጋ አስከፍለዋል ብለዋል።
በአፍሪካ እየተፈጠሩ ያሉ የሽብር ቡድኖችን ፣ሽብርተኞችን፣አህጉራዊ ና ቀጠናዊ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት አፍሪካውያን ቀወታደራዊና ደህንነት ዘርፎች በትብብር መሠራት አለባቸው ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።
አሁን የምንወስናቸው ውሳኔዎች ቀጣይ እጣፈንታችን በአለም አቀፍ ደረጃ ይወስናል ያሉት አቶ ተመስገን ጥሩነህ አጀንዳ 2063 እውን ለማድረግ የአፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል ምስረታ መፍጠን አለበት ብለዋል
በፋሲል ጌታቸው