
AMN- ጥር 15/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያና የፓኪስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ የሁለትዮሽና የባለ ብዙ ዘርፍ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የሚስችል የፖለቲካ ምክክር መግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
በሰምምነቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ጋር በግብርና፣ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በአቪዬሽን፣ በኢንዱስትሪ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ግንኙነቷን ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልፀዋል።
ስምምነቱ በአለም አቀፍና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል።
ስምምነቱን የፈረሙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና የፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ተቀዳሚ ምክትል ሚኒስትር አምባሳደር ሀሚድ አሽገር ከሃን ናቸው።
በፊርማ ስነ-ስርአቱ ላይ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እንደገለጹት ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ጋር በግብርና፣ በኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በአቪዬሽንና በሌሎችም ዘርፎች ያላትን ግንኙነት ማጠናከር ትፈልጋለች።
ስምምነቱ ሁለቱ ሃገራት በደቡብ ደቡብ ትብብር እንዲሁም በሁለትዮሽና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች አብረው ለመስራት የሚያስችላቸው መሆኑንም ገልፀዋል ፡፡
የፓኪስታን ተቀዳሚ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀሚድ አሽገር ከሃን በበኩላቸው የኢትዮጵያ እና የፓኪስታን ግንኙነት በሁሉም ዘርፎች እየተጠናከረ መምጣቱን ገልፀው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ጸጥታ እንዲረጋገጥ እያደረገች ያለውን ጥረት ማድነቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።