ኢትዮጵያና ፈረንሳይ የኢኮኖሚ ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

You are currently viewing ኢትዮጵያና ፈረንሳይ የኢኮኖሚ ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

AMN ህዳር 20/2017 ዓ.ም

የገንዘብ ሚኒስቴር ከፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ (ኤኤፍዲ) እና የፈረንሳይ ባለሙያዎች (ኤክስፐርቲስ ፍራንስ) ትብብርን ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ የኢኮኖሚ ትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ በኢኮኖሚ ልማት፣ በአየር ንብረት እርምጃ፣ በጤና እና በሰዎች ልማት ላይ ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን ባለሙያዎች በማሰባሰብ እና የህዝብ ፖሊሲዎችን በመደገፍ ላይ ያተኮረ መሆኑም ተመላክቷል።

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው “የኢትዮጵያ መንግስት የፈረንሳይ መንግስት ለሚያደርገው ድጋፍ ከፍ ያለ ዋጋ እንደሚሰጥ በመግለጽ፤ ይህ ስምምነት ትብብሩን የበለጠ እንደሚያሳድግ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

የፈረንሳይ ባለሙያዎች ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄረሚ ፔሌት ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል አድናቆታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ የወደፊቱን የትብብር መስኮች በማጉላት ገልጸዋል።

ሥራ አስፈፃሚው አክለውም ኤክስፐርት ፈረንሳይ በመንግስት ባለቤትነት ለተያዙት የድርጅት ማሻሻያ፣ የመንግስት-የግል አጋርነት እና አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሮች የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚያሰፋ አረጋግጠዋል።

በኢኮኖሚው ዘርፍ የእሴት ሰንሰለቶች፣ በብሔራዊ ቤተ መንግስት ውስጥ ያሉ ፕሮጀክቶች እና በጤናው ዘርፍ ባሉ ጉዳዮችም አፅንዖት ሰጥተዋል።

ፔሌት በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ያሉ ፕሮጀክቶችን በቅርበት ለመደገፍ እና በዲጂታል እና AI ቴክኖሎጂዎች ትብብርን ለማስፋት ቋሚ ቡድን ለማቋቋም እንዳቀዱ ማስታወቃቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review