ኢትዮጵያ የሱዳን ግጭትን ለመፍታት በሱዳናውያን የሚመራ የሰላም ሂደትን መደገፍ ቁልፍ መሆኑን ገለጸች

You are currently viewing ኢትዮጵያ የሱዳን ግጭትን ለመፍታት በሱዳናውያን የሚመራ የሰላም ሂደትን መደገፍ ቁልፍ መሆኑን ገለጸች

AMN-ሚያዚያ 7/2017 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የሱዳን ግጭት ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ በሱዳናውያን የሚመራ የሰላም ሂደትን መደገፍ እንደሚገባ አሳሰበች።

የሱዳን ጉዳይ መፍትሄ የሚያገኘው በሰላማዊ አማራጭ ብቻ ነው ስትልም ገልጻለች።

የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራን ያቀፈ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ዛሬ በለንደን ከተማ ሱዳንን አስመልክቶ በተካሄደ ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ ላይ ተሳትፈዋል።

ኮንፈረንሱ በእንግሊዝ፣ አውሮፓ ህብረት፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና የአፍሪካ ህብረት የጋራ አዘጋጅነት የተካሄደ ነው።

ከ14 ሀገራት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት በኮንፈረንሱ ላይ ተሳትፈዋል።

ኮንፈረንሱ ስለሱዳን የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት፣ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ እና ግጭቱ በፖለቲካዊ መንገድ እንዲፈታ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከሩን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ልዑክ በኮንፍረንሱ ላይ የሱዳን የሰላም ሂደት በሱዳናውያውን ባለቤትነት የሚመራ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የመፍትሄ ማፈላለግ ሂደት ሊሆን እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥቶ አንስቷል።

በፍጥነት ቋሚ የተኩስ አቁም ስምምነት በማድረግ የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ እና ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ሊኖር እንደሚገባም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ልዑክ ለሱዳን ሰላም ዓለም አቀፍ የተቀናጀ ጥረት እና አካሄድ እንደሚያስፈልግ ገልጾ ቀጣናዊ ተቋማት ከአጋሮች ጋር በመሆን በሱዳናውያን የሚመራ የፖለቲካ ሽግግር እንዲኖር መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review