ኤፍ ኤም 96.3 ራዲዮ የዘመኑን የላቀ ቴክኖሎጂ የያዘ የሬዲዮ ማሰራጫ ባለቤት ሊሆን ተቃርቧል ፡- አቶ ካሳሁን ጎንፋ

You are currently viewing ኤፍ ኤም 96.3 ራዲዮ የዘመኑን የላቀ ቴክኖሎጂ የያዘ የሬዲዮ ማሰራጫ ባለቤት ሊሆን ተቃርቧል ፡- አቶ ካሳሁን ጎንፋ

AMN – የካቲት 6/2017 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኤ ኤም ኤን) ኤፍ ኤም 96.3 የዘመኑን የላቀ ቴክኖሎጂን የያዘ የሬዲዮ ማሰራጫ ባለቤት ሊሆን መቃረቡን ዋና ስራ አስፈጻሚው አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገለፁ፡፡

በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ኤፍ ኤም 96.3 የአለም የሬዲዮ ቀን ተከብሯል።

የኤ ኤም ኤን ዋና ስራ አሴፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ፣ ኤ ኤም ኤን ኤፍ ኤም 96.3 በቅርቡ በሚገጠምለት ዘመኑን የሚመጥን የላቀ ቴክኖሎጅን የያዘ የሬዲዮ ማሰራጫ እንደሚሆንና በተሻለ የስርጭት ጥራት ለአድማጮች እንደሚደርስ ገልፀዋል።

ዘመናዊው የሬዲዮ ማሰራጫ በአጭር ጊዜ ስራ ሲጀምር ኤፍ ኤም 96.3 ሬዲዮ የተደራሽነት ችግሩን ሙሉ ለሙሉ የሚቀርፍ እና ተደማጭነቱን ለማላቅም እንደሚያስችለው ነው አቶ ካሳሁን የገለጹት፡፡

የትውልድ ድምጽ የሆነውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ኤፍኤም 96.3 ራዲዮ ምርጫቸው አድርገው እየተከታተሉ ላሉ አድማጮች ምስጋና ያቀረቡት ዋና ስራ አስፈፃሚው በቅርቡ ተደራሽነቱን በማስፋት የምስራች ይዞ እንደሚቀርብም ቃል ገብተዋል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የቀድሞ የሬዲዮ ጣብያው ጋዜጠኞች ትዝታቸውን ለአድማጮች አካፍለዋል፡፡

በአይናለም አባይነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review