‎እንደ ሀገር ጠቀሜታ ባላቸውና ለቱሪስት ምቹ በሆኑ ከተሞች ላይ የሚሰሩ ትላልቅ የኢንቨስትመንት ስራዎችን ማጠናከር ይጠበቃል-ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ

AMN-ታህሣሥ 6/2017 ዓ.ም

‎የቱሪዝም ሚኒስተር ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ፣ በሐዋሳና አካባቢው የሚገኙ መሰረተ ልማትና በቱሪዝም ዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ጉብኝተዋል።

‎ሚኒስትሯ በሐዋሳና ዙሪያ አካባቢ እየለማ ያለው ሰፋፊ የመስኖ መሰረተ ልማት ስራ የሚበረታታ መሆኑን ገልጸዋል።

‎ይህ በግለሰብም ሆነ በማህበራት የሚተገበረው የልማት ስራ እንደ ሀገርም ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ጠቁመዋል።

‎በዓመት 2 እና 3 ጊዜ ሰብልን የማምረት በተለይም የፍራፍሬ ምርቶች ላይ ትኩረት መሰጠቱን ያነሱት ሚኒስትሯ በክልሉም በከፍተኛ ወጪ የተሰራ የመስኖ መሰረተ ልማት ስራ በሺዎች የሚቆጠሩ አርሶአደሮችን ተጠቃሚ ያደረገና ምርቱንም ወደ ሌሎች ከተማዎች ጭምር መውሰድ የተቻለበት ስለመሆኑ ገልጸዋል።

‎በከተማዋ በአዲስ መልክ እየተገነቡ ያሉ የሪዞርቶችና ሆቴሎች ግንባታ ፣ በሀይቁ ዙሪያ የሚገነቡትን ጨምሮ ከተማዋን የቱሪስት መዳረሻ ከማድረግ አኳያ የላቀ ፋይዳ ያላቸው መሆኑን ጠቁመዋል።

‎እንደ ሀገርም እየተሰራ ላለው ኮንፍረንስ ቱሪዝም ትልቅ አቅም የሚፈጥርና ለከተማዋም አዲስ የቱሪዝም መዳረሻን የሚያስገኝ በመሆኑ ከክልሉ ባለሀብትም ብዙ ይጠበቃል ብለዋል።

‎ለአርሶ አደሩ የተሻለ የገበያ ትስስር መፍጠር እንደሚገባ የተናገሩት ሚኒስትሯ በአዲስ መልክ እየተገነባ ያለውን የሴንትራል ሪዞርት እና ወተር ፓርክ መጎብኘታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review