
እግረኞች በተፈቀደላቸው የእግረኛ መንገድ ብቻ መጓዝ እንደሚኖርባቸው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስገነዘበ
AMN – ሀምሌ 8/2016 ዓ.ም
በኮሪደር ልማቱ በተገነቡ መሰረተ ልማቶች ስንገለገል እግረኞች በተፈቀደው የእግረኛ መንገድ ብቻ መጓዝ እንደሚኖርባቸው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስገነዘበ፡፡
የታክሲ አሽከርካሪዎችም ለልማት የተሰራው ኮሪደር ልማት ላይ እና ሳር የተተከለባቸው ቦታዎች ተሳፋሪን ማውረድ ፤መጫን እና መኪና ማቆም የተከለከለ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ከኮሪደር ልማት ጋር ተያይዞ የተሰሩ የልማት ስራዎችን መጠበቅ እና መንከባከብ የሁላችን ግዴታ በመሆኑ አሽከርካሪዎች ሳፋሪዎችን ለመጫንም ለማውረድም መሻገሪያ ቦታን ብቻ እንዲጠቀሙ መልእክት ተላልፏል፡፡
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!