
AMN-ኅዳር 5/2017 ዓ.ም
በቅርቡ የፀደቀውን የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅን መሠረት በማድረግ በተዘጋጀው የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ላይ ከሁሉም የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡
ውይይቱን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ፣ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ለተቋማትና የስራ ኃላፊዎች የመወስን አቅም ከተጠያቂነት ጋር አጣምሮ የሚሰጥ መሆኑን አመልክተዋል።
የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ግዢ የሚፈጽሙ በመሆናቸው ከዚህ ቀደም ሲያነሱቸው የነበሩ የግዢ ችግሮችን ለመፍታት እንዲየግዝ ተደረጎ ረቂቅ መመሪያው መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
ሚኒስትሩ ረቂቅ መመሪያው ዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው፣ ተገቢ ቁጥጥር ለማስፈንና በማዕከላዊነት ለማስተባበር የሚያስችል ሆኖ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መመሪያው ይበልጥ እንዲዳብር የበኩላቸውን የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ማሳሰባቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡