ኮሚሽኑ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት ከ12 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን አስታወቀ

You are currently viewing ኮሚሽኑ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት ከ12 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን አስታወቀ

AMN- መስከረም 27/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ የህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት ከ12 ቢሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ የ2016 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተንኩዌይ ጆክ በ2016 ዓ,ም ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ማዳን መቻሉን ተናግረዋል።

ከ6 ሺ 700 በላይ ቤቶችን አድሰውና ገንብተው ለቅመ ደካማ የከተማዋ ነዋሪዎች ማስረከባቸውን ተናግረዋል።

ከ28 በላይ ከሆኑ ተቋማት ጋር በቅንጅት መሠራቱንም አመላክተዋል።

የበጎ ፍቃድ ስራ በቅንጅት መስራት ይጠይቃል ያሉት ኮሚሽነሩ ለዚህ ስራ ማህበረሰቡም እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

ከተለያዩ ተቋማት የመጡ ባለድርሻ አካላት አስተያየቶች የተነሱ ሲሆን በ2016 ደካማ የነበሩ አፈፃፀሞችን በላቀ አፈፃፀም በመተካት ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን በ2016 ዓ,ም በቅንጅታዊ ስራው ጥሩ አፈፃፀም ለነበራቸው ተቋማት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

2017 ዓ.ም የቅንጅት ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል የትስስር ሰነድ ፊርማ መርሃ ግብርም ተከናውኗል።

በመሀመድ ኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review