የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎታቸውን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የጀመሩት ስራ የሚደነቅ ነው -የሃይማኖት አባቶች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች

You are currently viewing የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎታቸውን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የጀመሩት ስራ የሚደነቅ ነው -የሃይማኖት አባቶች እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች

AMN – ጥር- 23/2017 ዓ.ም

ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ፣ ባለሀብቶች እና የሃይማኖት አባቶች የአዲስ አበባ ከተማን የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ጎብኝተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ጉብኝት ያደረጉት ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና የሃይማኖት አባቶች፣ ተቋሙ ዘመኑን የዋጀ ዘመናዊ አሰራርን እየተከተለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የመዲናዋ ተቋማት በተጨባጭ ለህዝብ ግልጋሎት ምቹ ሆነው እየተገነቡ ስለመሆኑ ማሳያ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሌላኛው በመዲናዋ በትኩረት የሚሰራው የሰው ተኮር ልማት ስራ፣ በመዲናዋ ከልማት ጎን ለጎን የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱ ስራዎች እየተሰሩ ለመሆኑ ማሳያ መሆኑን በጉለሌ የተቀናጀ የልማት ፕሮጀክቶች ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ጠቁመዋል፡፡

ታሪክን ከዘመናዊነት ጋር አዋህዳ በልማት ጎዳና ላይ እያመራች ያለችው አዲስ አበባ የብሄራዊ ቤተመንግስት እና ሌሎች የቱሪዝም መዳረሻዎችን የማልማት እና የማደስ ስራን መስራቷን አንስተዋል፡፡

በብሄራዊ ቤተመንግስት ጉብኝት ያደረጉ ጎብኚዎቹ ብሄራዊ ቤተመንግስት በታሪክ ውስጥ ልማትን፤ በልማት ውስጥ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን እውን የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

በመዲናዋ የሚሰሩ የልማት ስራዎች ጥራት እና ፍጥነትን ታሳቢ ያደረጉ እና የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስለመሆኑ የሃይማኖት አባቶች ፣ ባለሀብቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች ተናግረዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review