የመድሃኒት አቅርቦት ዘርፉ ቀጣይነት ያለው እና አስተማማኝ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት አስታወቀ።

You are currently viewing የመድሃኒት አቅርቦት ዘርፉ ቀጣይነት ያለው እና አስተማማኝ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት አስታወቀ።
  • Post category:ጤና

አገልግሎቱ ያዘጋጀው 3ኛው አለም አቀፍ የመድሃኒት አቅርቦት ፎረም እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ በፎረሙ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት የፎረሙ አላማ በመድሃኒት አቅርቦት ሰንሰለቱ ካሉ አካላት ጋር ያለን ግንኙነት ለማጠናከር እና አቅርቦቱን ቀጣይነት ያለው እና አስተማማኝ ማድረግ ነው።

በሀገር ውስጥ ያለውን የመድሃኒት እና የህክምና ግብዓቶች ኢንቨስትመንት አማራጮች በማስተዋወቅ እና አለም አቀፍ አምራቾች በዘርፉ ኢንቨስትመንት በስፋት እንዲሰማሩ በማስቻል ከውጭ የሚገባውን ምርት በሀገር ውስጥ ምርቶች መተካትም ሌለኛው አላማው መሆኑን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት።

83 በመቶ የሚሆነው የመድሃኒት አቅርቦት በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅርቦት አገልግሎት በኩል የሚፈጸም ሲሆን ባለፉት አምስት አመታት ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው መድሃኒቶቾ ተገዝተው ወደ ሀገር ውስጥ መግባታቸው ተገልጿል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review