AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም
የምዕራብ ዕዝ አብዲሳ አጋ ክፍለጦር በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን ጉድሩ ወረዳ ሲንቀሳቀስ በነበረው ፅንፈኛ ቡድን ላይ በወሰደው የማያዳግም እርምጃ ከአርባ አራት በላይ ፅንፈኞች ላይ ርምጃ ወስዷል፡፡
ከፅንፈኛው እጅ ተተኳሽ እና መሳሪያ እንዲሁም ቦንብ እና የወገብ ትጥቅ በሠራዊቱ ቁጥጥር ስር መዋሉም ተገልጿል።
ፅንፈኛ ቡድኑ የህዝብን ሰላምና ልማት የሚያደናቀፍ አላማ ቢስ የጥፋት ሃይል በመሆኑ ሠራዊቱ መግቢያና መውጫውን እየተከታተለ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የሬጅመንቷ ዋና አዛዥ ሻለቃ ጨርቆስ ሃጎስ ተናግረዋል።

ሠራዊቱ የቆመለትን አላማ ጠንቅቆ የሚያውቅና ግዳጁን በጀግንነት የሚወጣ በመሆኑ የተገኘው ድል በአመራርና አባላቱ በተቀናጀ መንገድ በተሰራ ስራ የመጣ ውጤት መሆኑ ተመልክቷል።
ህገ-ወጥ ቡድኑ ከዚህ ቀደም የአካባቢውን ሰላም ሲያውክና ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሰቆቃ በትር ሲያሳርፍ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በሠራዊቱ ጥብቅ ክትትል አንፃራዊ ሰላም ማስፈን መቻሉን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።