የሰው ልጅን የዕለት ተዕለት ተግባር የምታከናውን ደስታ የተሰኘች ሮቦት ነገ ለዕይታ ትቀርባለች

AMN – ሚያዝያ 1/2016 ዓ.ም

ደስታ የሚል ስያሜ የተሰጣት እና የሰው ልጅ በዕለት ተዕለት ውሎው የሚያከውነውን ተግባር መፈጸም የምትችል ሮቦት ነገ ረቡዕ ሚያዝያ 2 ከረፋዱ 5:00 ጀምሮ ለዕይታ ትቀርባለች።

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ዘውዴ ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ሚዲያ እንደገለጹት፣ ደስታ በዓለም ላይ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ እንዲሁም የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ የደረሰበትን አና ወደፊት የሚደርስበትን እውቀት በሳይንስ ሙዚየም ታስረዳለች።

ከተመልካች ለሚቀርብላት ጥያቄም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ቋንቋዎች ምላሽ እንደምትሰጥም ተነግሮላታል።

ደስታ በጃዝ ሙዚቃ ትደሰታለች፣ ትዝናናለችም፤ ከዚህም ባሻገር ራሷን ችላ የምትንቀሳቀስ ሲሆን ራይድ ጠርታም ትጓዛለች ተብሏል።

ደስታ ሮቦት ረቡዕ ሚያዝያ 2 እና ሐሙስ ሚያዝያ 3 የተለያዩ ዝግጅቶች ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ የጃዝ ሙዚቃ በመጫወት አስደናቂነቷን ታስመሰክራለችም ተብሎ ይጠበቃል።

በሀገር ውስጥ እና በውጭ ባለሙያዎች የተሠራችው ሮቦት ነገ በሳይንስ ሙዚየም የምታቀርበውን ኹነት በጋራ እንዳዘጋጁት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ iCog Lab እና RIDE መሆናቸው ተገልጿል።

በአዕምሮ ዐቢይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review