የባሕር ዳር ከተማ የሠላም አስከባሪ አባላት ተመረቁ

You are currently viewing የባሕር ዳር ከተማ የሠላም አስከባሪ አባላት ተመረቁ

AMN-ጥር 4/2017 ዓ.ም

በባሕር ዳር ከተማ በወታደራዊ ግዳጅ አፈጻጸም የሰለጠኑ የሠላም አስከባሪ አባላት ተመረቁ።

የባሕርዳር ከተማን ሰላምና ፀጥታን በዘላቂነት የማፅናቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

የሠላም አስከባሪ አባላት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የአስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪና የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው እና የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ ሌሎችም አመራር አባላት በተገኙበት ተመርቀዋል።

የሰላም አስከባሪ አባላቱ የከተማውን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚያስችልና በተግባር የተደገፈ በቂ ወታደራዊ ስልጠና የወሰዱ መሆናቸው ተመላክቷል።

የሰላም አስከባሪዎችን አቅም በማጎልበት የከተማውን ሰላምና ፀጥታን በዘላቂነት የማፅናቱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።

በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በየአካባቢው የሰላም አስክባሪ አባላትን አቅም የመገንባትና ክህሎታቸውን የማሳደግ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል ።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review