78ተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ “ሰላም ፣ብልፅግና፣ ለውጥና ዘላቂነት” በሚል መሪ ሀሳብ በኒው ዮርክ መካሄዱን ቀጥሏል።
የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከጉባኤው ጎን ለጎን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ኢትዮጵያ ያሉባትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች ለመፍታት እያደረገች ባለው ጥረት ስኬታማ እንድትሆን ተመኝተዋል።
ተመድ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በባለ ብዙ ወገን የትብብር ስርዓት ቁልፍ ሚና ያላት አገር ናት ብለዋል ዋና ፀሐፊው።
አቶ ደመቀ ተመድ እና ዋና ፀሐፊው በግል ጥረታቸው ለኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ወቅቶች ያደረጉትን ድጋፍ አድንቀዋል።
አቶ ደመቀ ለአንቶኒዮ ጉቴሬዝ የሰላም ስምምነቱን ትግበራ አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።
ድርጅቱ የመልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም ጥረቶችን እንዲሁም ሌሎች የሰብዓዊ ጉዳዮች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr
Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9
Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8
Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ