የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(ዩኒዶ) ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጎልበት እንደሚፈልግ የድርጀቱ ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር አስታውቀዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኒው ዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 78ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(ዩኒዶ) ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም ዳይሬክተር ጀነራሉ ዩኒዶ የኢትዮጵያን የልማት ፕሮጀክቶች ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑንና የኢትዮጵያ ሰላም፣መረጋጋትና ልማት ቀዳሚ ትኩረቶች እንደሆኑ ገልጸዋል።
ድርጅቱ ዓለም አቀፍ ጉባኤውን እ.እ.አ በሕዳር ወር 2023 በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ ዳይሬክተር ጀነራሉ ለአቶ ደመቀ ገልጸውላቸዋል፡፡
አቶ ደመቀ ዳይሬክተር ጀነራሉ በግላቸው እያደረጓቸው ላሉት ጥረቶች ምስጋናቸውን አቅርበው ኢትዮጵያ ከዩኒዶ ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንዲኖራት ትፈልጋለች ብለዋል።
በተጨማሪም አቶ ደመቀ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከአውሮፓና መካከለኛው ምስራቅ አገራት መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr
Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9
Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8
Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ