AMN- መስከረም 22/2017 ዓ.ም
የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን በቱሪዝሙ ዘርፍ ምቹ ስነምህዳርን መፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት እና ኤግዚቢሽን አካሂዷል።
በውይይቱ እና በኤግዚቢሸኑ ላይ ከፍተኛ የፌደራልና የክልሉ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት እና የሚመለከታቸው የግል እና የመንግስት ተቋማት እንዲሁም ከአጎራባች ሀገራት የመጡ የውጪ ሀገር ዜጎች ተሳትፈዋል ።
የቱሪዝሙን ዘረፍ ለማነቃቃትና ለማስተዋወቅ እንደ ኢሬቻ ያሉ የአደባባይ በዓላት ትልቁን ድርሻ እንደሚይዙ በመድረኩ የተነሳ ሲሆን ይህ የተሳካ እንዲሆን ከክልሎች እና ከሌሎች የዓለም ሀገራት ተሞክሮን መውሰድ እና በቅንጅት መስራት አስፈላጊ ስለመሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ የብዙ ተፈጥሯዊ ፣ታሪካዊ እና ባህላዊ የቱሪዝም መስዕቦች ባለቤት ብትሆንም ያንን አውቆ የገቢ ምንጭ ከማድረግ አንፃር ክፍተቶች እንዳሉ ተጠቁሟል፡፡
ይህንን ለመጠቀም በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም ነው የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን በመድረኩ ያስታወቀው።
ኢሬቻ በቱሪዝሙ ዘርፍ ያለው ኢኮሎሚያዊ ፍይዳ ከፍተኛ ስለመሆኑም በመድረኩ ተገልጿል፡፡
በራሄል አበበ