AMN – ታኅሣሥ 20/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ( ዶ/ር ) የታላቁ ቤተመንግሥት እድሳት የታሪክ እና የባሕል ቅርሳችንን ጠብቆ ለማቆየት የምናደርገው ጥረት ከፍ ያለ ርምጃ ነው ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ፅህፈት ቤቱ በመረጃው የተጀመረው የእድሳት ተግባር አሁን አንድነት ፓርክ ከሆነው ከታላቁ ቤተመንግሥት ጀምሮ ይኽን ትእምርታዊ ስፍራ እንደገና ለታላቅ አገልግሎት እንዲሰናዳ በማድረግ ቀጥሏልም ብሏል።
ታላቁ ቤተመንግሥት አሁን የሕዝባችንን ጽናት፣ ጥበባዊ አቅምና ርዕይ ግዘፍ ነስቶ የሚታይበት የሀገራዊ ጉዟችን ዋቢ ሆኖ ይታያል።
የቀደመ ግዝፈቱን እና ውበቱን በመመለስ ያለፈ ታሪካችንን እናከብራለንም ብሏል።
ለትውልዶችም የኩራትና የተነሳሽነት ዘላቂ ተምሳሌት አኑረናል።
እንሆ የቤተመንግሥት ሙዝየም ለሁሉም ሆኗል ሲልም ነው ጽሕፈት ቤት በመረጃው ያመለከተው፡፡