AMN-ነሐሴ 19/2016 ዓ.ም
የታላቁ ኅዳሴ ግድብ የውሃ ማስተንፈሻ በሮች ተከፍተው ተጨማሪ 2 ሺ 800 ሜኪ ውሃ በሰከንድ ማፍሰስ መጀመራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፣ ወደታችኛው የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ተጨማሪ ብስራት ከጉባ መደመጡን በማኀበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል።
የወንዝ ፍሰት ሳይስተጓጎል ከመቀጠሉም በተጨማሪ የግድቡ የውሃ ማስተንፈሻ በሮች ተከፍተው ተጨማሪ 2 ሺ 800 ሜኪ ውሃ በሰከንድ ማፍሰስ ጀምረዋል ብለዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የውሃ ፍሰትን በመቆጣጠር፣ የጎርፍ አደጋ ስጋትን በመቀነስ፣ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በተለይ በድርቅ ዘመን መጠኑ ያልዋዠቀ የውሃ አቅርቦት እንዲደርሳቸው ያደርጋል ብለዋል።
ይህ የተመዘነና የተመጣጠነ የውሃ ልቀት ግብርናን፣ የኃይል የማመንጨት ሥራን፣ በቀጠናው ያለ የሀብት አጠቃቀም ምጣኔን ለማጎልበት በእጅጉ እንደሚጠቅም ገልጸዋል።