AMN-ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አዲስ አርማ (ሎጎ) ይፋ አድርጓል።
ሚኒስቴሩ እያካሄደ ያለው ስር ነቀል ተቋማዊ ሪፎርም አካል የሆነው የኤርጎኖሚክስና የስራ ከባቢን ለሰራተኞችና ለተገልጋይ ምቹ ከማድረግ ጎን ለጎን የብራንዲንግ ስራዎችን ከመስሪያቤቱ ተልዕኮ ጋር አያይዞ በመስራት ላይ እንደሚገኝ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ገልጸዋል::
በዚሁ መሰረት እስካሁን ሲገለገልበት ከነበረው ሎጎ በተሻለ የመስሪያቤቱን ዋና መስሪያቤት ህንፃ እና ሀገራዊና አለም አቀፋዊ የገበያ ትስስርን መነሻ ያደረገ ለማስታወስ ቀላል እና የሚታወስ ሎጎ መዘጋጀቱን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል::