AMN – የካቲት 4/2017 ዓ.ም
የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፤ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን ፤9ኛ መደበኛ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ።
ምክር ቤቱ ጉባኤውን ማካሄድ የጀመረው የ8ኛ መደበኛ ቃለ- ጉባኤን በማጽደቅ ነው።
ከዛሬ ጀምሮ እስከ የካቲት 7/2017 ዓ.ም የሚካሄደው የምክር ቤቱ ጉባኤ በቆይታው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ እንደሚመክር ከመርሃ ግብሩ መረዳት ተችሏል።
ከዚህም ውስጥ የክልሉ የአስፈፃሚ አካላት የ2017 ግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ በስፋት በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ይገኙበታል።
እንዲሁም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የግማሽ ዓመት ሪፖርት፣ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ኦዲት ላይ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚያስቀመጥም ይጠበቃል።
በተጨማሪም በሚቀርቡ የተለያዩ አዋጆች ላይ ምክር ቤቱ በስፋት በመምከር ሹመቶችን በማጽደቅ እንደሚጠናቀቅ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።