የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 3ኛውን ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ ለማዘጋጀት የሰላም ዋንጫ ተረከበ

You are currently viewing የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 3ኛውን ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ ለማዘጋጀት የሰላም ዋንጫ ተረከበ

AMN – ሚያዝያ 01/2017

“የሃይማኖት ተቋማት ለሁለንተናዊ ሰላም እና ዕርቅ” በሚል መሪ ሐሳብ በኦሮሚያ ክልል፣ ጅማ ከተማ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 2ኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ በዛሬው ዕለት በሰላም ዋንጫ ርክክብ ተጠናቅቋል።

የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 3ኛውን ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ በአማራ ክልል ለማካሄድ የሁለተኛው ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ አዘጋጅ ከሆነው ከኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሰላም ዋንጫ በክብር ተረክቧል።

ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኦሮሚያ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።

የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ በቂ ዝግጅት በማድረግ ሦስተኛውን አገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ በድምቀት በአማራ ክልል ለማካሄድ የሚሠራ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል።

የሰላም ጉባኤው ሁሉም ቤተእምነቶች ለሀገር ሰላም ገንቢ ሚና በማጫወት ኃለፊነታቸውን መጫወት እንዲችሉ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የማኅበራዊ ትሥሥር ገፅ የተገኘው መጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review