የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በሳይንሳዊ መንገድ ለማልማት እየተሰራ ነው፡- የአዲስ አበባ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ

You are currently viewing የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን በሳይንሳዊ መንገድ ለማልማት እየተሰራ ነው፡- የአዲስ አበባ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ

AMN-መስከረም 22/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የአረንጓዴ ልማት ስራዎች የበለጠ ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ በሳይንስና በእውቀት የታገዙ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው በዘርፉ ለተሰማሩ አካላት ስልጠና ሰጥቷል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ደረጃዋን የጠበቀችና ለነዋሪዎች የተመቸች ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል፡፡

በከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ስራ ላይ የተሰማሩ ማህበራትን ስራዎች በእውቀት የታገዙና ሳይንሳዊ ማድረግ የበለጠ ውጤት እንዲገኝ ያግዛል፡፡፡፡

ይህን ልምድና ወጥ ያልሆነ የአረንጓዴ ልማት ጥበቃ ስራን ለማዘመን የአዲስ አበባ የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ በዘርፉ ለተሰማሩ ማህበራትና አባሎቻቸው ስልጠና መሰጠቱን የቢሮው ኃላፊ ይመኙሻል ታደሰ ገልፀዋል፡፡

በመዲናዋ እየተከናወኑ ያሉ የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ሳይንሳዊ ሂደቱን በጠበቀ መልኩ መንከባከብ እንዲቻል ስልጠናው እንዳገዛቸው ሰልጣኞቹ ተናግረዋል፡፡

በንፋስ ስልክ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተሰጠው ይሄ ስልጠና በከተማዋ በሚገኙ ስድስት የተመረጡ የሙያና ቴክኒክ ኮሌጆች በክላስተር በተመሳሳይ ጊዜ የተሰጠ ሲሆን በተለይ በአመለካከት እና ቢሮዉና ማህበራቱ በተዋዋሉበት የህግ ማዕቀፍ ዙሪያ ግልፅ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ የሚያስችል መሆኑ ተገልጻል፡፡

በሄለን ጀምበሬ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review