AMN – መጋቢት 2/2017 ዓ.ም
በዚህም የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዛሬ ምሽት አንፊልድ ላይ የመልሱን ጨዋታ ከፒ ኤስ ጂ ጋር ያደርጋል፡፡
በዚህ ዓመት በአንፊልድ ስታድዬም በኖቲንግሃም ፎረስት ብቻ የተሸነፈው ሊቨርፑል ዛሬ ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ ከባድ ፍጥጫ ይጠብቀዋል፡፡
በፓሪሱ ጨዋታ ከፍተኛ ብልጫ የወሰዱት የፒ ኤስ ጂው አሰልጣኝ ሊዊስ ኢንሪኬ፣ የዛሬ ምሽቱን የመልስ ጨዋታ አሸንፈው በደርሶ መልስ ድምር ውጤት ልቀው ሩብ ፍጻሜ እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡
ሆላንዳዊ የሊቨርፑል አቻቸው አርን ስሎትም ቢሆኑ ተጋጣሚያቸው ፒ ኤስ ጂ የዓለማችን ምርጥ ቡድን መሆኑን አልሸሸጉም፡፡
የጣሊያኑ ኢንተር ሚላን በተመሳሳይ ከምሽቱ 5 ሰዓት ከኔዘርላንዱ ፌይኖርድ ጋር ሳንሴሮ ላይ ይጫወታል፡፡
ሙኒክ ሰፊ የማለፍ እድል ይዞ ከባየር ሊቨርኩሰን ጋር ይጫወታል፡፡
ለምሽት ሶስት ሰዓት ሩብ ጉዳይ የሚጀምረው የባርሴሎና እና ቤኔፊካ የዛሬ የመክፈቻ ጨዋታ ነው፡፡
ባለፈው ሳምንት ፖርቹጋል ላይ ያደረጉትን ጨዋታ ባርሴሎና በራፊና ብቸኛ ግብ 1ለ0 ማሸነፉ አይዘነጋም፡፡
የካታሎኑ ክለብ በሐኪሙ ድንገተኛ ህልፈት ምክንያት ቅዳሜ ምሽት ከኦሳሱና ጋር ሊያደርገው የነበረውን የስፔን ላሊጋ ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ማራዘሙ የሚታወስ ነው፡፡
በታምራት አበራ