የአውሮፓ ኅብረት የአንካራ ሥምምነትን እንደሚደግፍ አስታወቀ

AMN – ታኅሣሥ -3/2017 ዓ.ም

የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያና ሶማልያ መካከል የተደረሰውን የአንካራ ሥምምነት እንደሚደግፍ አስታወቀ።

ሥምምነት በአፍሪካ ቀንድ ያለውን ውጥረት ከማርገብ ባለፈ የመከባበር እና የመነጋገርን አስፈላጊነት የሚያንፀባርቅ መሆኑን ኅብረቱ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በሁለቱ ሀገራት አንድነትና ሉዓላዊነት የጠበቀ ብሎም በዓለም አቀፍ ሕግ የተቀመጡ መርሆችን ያከበረ ስምምነትን የአውሮፓ ኅብረት እንደሚደግፍ አረጋግጧል።

ኢትዮጵያና ሶማልያ ሥምምነት ላይ እንዲደርሱ ቱርኪዬ የተጫወተችውን ጠቃሚ ሚና ኅብረቱ እውቅና ሰጥቷል።

የአውሮፓ ኅብረት ሁለቱ ሀገራት የሚያደርርጓቸውን ቀጣይ ውይይቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑንም አስታውቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review