AMN – ህዳር 2/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የታየዉ የአሰራር ሪፎርም እና ባለፉት ወራት እቅዶችን ለማሳካት የሰራቸዉ ተግባራት የሚበረታቱ መሆናቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሬት እና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
በአዲስ አበባ ምክር ቤት መሬት እና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ያለፉት ወራት የስራ እንቅስቃሴ እና የእቅድ አፈፃፀምን እየገመገመ ነዉ፡፡
በምክር ቤቱ የመሬት እና ግንባታ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ኒዕመተላህ ከበደ፤ ኮርፖሬሽኑ ቤቶችን በአግባቡ ለማስተናገድ እና አገልግሎቱን የተሳለጠ ለማድረግ እየሰራ ያለዉ ስራ የሚበረታታ ነዉ ብለዋል፡፡
በግምገማዉም በቀጣይ መጠናከር እና መታረም ባለባቸዉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ምክክር እንደተደረገ ነዉ፡፡
በተመስገን ይመር