የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅምን ለማሳደግ እንደሚሠራ ገለፀ

You are currently viewing የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅምን ለማሳደግ እንደሚሠራ ገለፀ

AMN- መስከረም 20/2017 ዓ.ም

አካዳሚው የ2017 በጀት ዓመት የስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል።

በስልጠና ማስጀመሪያ መርሀግብር ላይ መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር ) በ2016 በጀት ዓመት በስልጠናዎች የመጡ ዘርፈ ብዙ ለውጦች መኖራቸውን ተናግረው በ2017 በጀት ዓመት ከ13 ሺ በላይ አመራሮችንና ባለሙያዎችን ለማሰልጠን መታቀዱን ገልፀዋል።

የአመራር አካዳሚው በስልጠና ማስጀመሪያ መርሀግብሩ የአዲስ አበባ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ሰራተኞችን ና አመራሮችን በማሰልጠን ጀምሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ በ2016 እና በ2017 ቢሮው ለአመራሩና ባለሙያዎቹ ስልጠና ለመስጠት ዕቅድ መያዙን ገልፀዋል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review